እንኳን ደህና መጡ

አብክመ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ

የቢሮ  ኃላፊ መልዕክት

የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ  ኃላፊ መልዕክት

የምንመራው የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮም በከተሞች ጉዳይ ላይ ቁልፍ ሚና ያለውና ከተሞች የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ለውጥ ሞተርና ማዕከል፣ ውብና ጽዱ፣ ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ በማስቻል ለክልላችን ብሎም ለአገራችን ብልፅግና ወሳኝ የሆኑ ተግባራት የሚከናወኑበት ነው፡፡ በመሆኑም ቢሮው የክልሉ ከተሞች  መሰረተ ልማት የተስፋፋባቸው፣ ውብና ፅዱ፣ የልማትና የአገልግሎት ማዕከል እንዲሆኑ በመገንባት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን እንደ ተልዕኮ ይዞ ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

  በአሁኑ ወቅት በክልላችን በየአካባቢው አዳዲስ ከተሞች መፈጠር፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት እና የነባር ከተሞች ወደ ጎን መስፋት ከተፈጥሮዓዊው የህዝብ ዕድገት ጋር ተዳምሮ የከተሞች ህዝብ ብዛት ከሚጠበቀው በላይ በፍጥነት የጨመረበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይህን  ተከትሎም በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጡ ተደራሽ እና አርኪ ያልሆነበት፣ ሌብነት በስፋት የሚስተዋልበት፣ የመኖሪያ ቤት እና የመሰረተ ልማት ፋላጎት በእጅጉ የጨመረበት እንዲሁም ሥራ አጥነት እና የከተማ ድህነት የተስፋፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በተለይም በከተሞች የሚታየውን ሌብነት መታገል እና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ልዩ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ነው፡፡

ሞላ መልካሙ (ዶ/ር)

የአብክመ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

የተመረጡ አገልግሎቶች

አዳዲስ ዜናዎች

“አመራሩና ፈጻሚው በክረምት ወራት የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ብቻ ከማተኮር ወጥቶ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ እያደረገ ያለው የተግባር ምላሽ አበረታች ነው”

አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ አመራሩና ፈጻሚው በክረምት ወራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ...

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በፋሲሎ፣ በየካቲት 23 እና በዶና በር ትምህርት ቤቶች ያስገነባቸውን 5 ብሎክ 20 አዳዲስ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ገንብቶ አስመረቀ፡፡

በምርቃ ፕሮግራሙ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ...

በአማራ ክልል በየዓመቱ በአማካኝ 975 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ለመኖሪያ ቦታ እየተሰጠ ነው።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ለተደራጁ የብሎክ እጣ የማውጣት መርሐ ግብር እያካሄደ ነው። የባሕር ዳር ከተማ...

የመርዓዊ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተመረቀ!

በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር የተገነባው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስን ጨምሮ የክልልና የሰሜን ጎጃም ዞን...

የቢሮው አስተዳደሮች

ሞላ መልካሙ (ዶ/ር)

የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሱለይማን እሸቱ

ምክትል ቢሮ ኃላፊ

አቶ አላምር ተሻለ

የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ

አቶ ሺቤ ክንዴ

የቢሮ አማካሪ

አዲሱ ደባልቄ (ዶ/ር)

በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

በክልላችን የሚገኙ ከተሞች

1

በክልሉ ከሚገኙ 60,560 የመንግስት ቤቶች ውስጥ ቤቶች ወደ ዘመናዊ የመረጃ ቋት (ሶፍትዌር) የገቡ

1

በዘርፉ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸዉ

1

ያግኙን

Scroll to Top